ጀባ᎕ጀባ
ሀግስ ለግስ ሀራም
ንግስና በፓልቶክ አለም
ፈላጩ ቆራጩ እንዳው እሱ ብቻ
ሻሞ ብሎ ሰጥቶ መከጀል ለብቻ
ማንም ሳይማከር ሳይለካ ሚዛን
ጀባ ብሎ ሰጥቶ የኡማውን ሃዘን
አከሌ አምባሳደር የኡማው ተወካይ
አከሌ ጠቢብ ነው ለችግሩ አምካይ
ኧረ በምን ሂሳብ በማን ምስካሪ
የኡማውን ጉዳይ ሰጥተን ለስም ኖሪ
እሱ ጎታች ሆኖ ጋሪና ፈረሱን
በድቅድቅ ጨለማ ሳያሳየው ፊቱን
አመሳቅሎ ቆሞ የሚሄድ ቢመስለው
ማን ያነቃው ይሆን ፈረሱ ሳይረግጠው?
No comments:
Post a Comment