Thursday, March 26, 2009

wey-EMNET

ወይ እምነት!!

እምነት ብ ሎ ማለት
የሚኖሩ ለት
ሳይኖሩ የኖሩ
ሳያምኑ ያስተማሩ
ምላሳቸው አማኝ
ተግባራቸው ኮናኝ
የሱን ዘዴ ንቀን
በኛ እውሸት ሞልተን
ወይ እምነት!!
ፈጣሪ ፈጠረን ሊያሳይ ታምሩን
እኛ ከሱ በላይ ልናሳይ መገዱን
ለማናውቀው አለም እንዲሁ ተጨቃጭቀን
ማመንስ እንዲህ ነው መውደድስ እንዲህ ነው
መከራ የማይፈታው ትልቁ ተግባር ነው
ወይ እምነት!!
አማኝ ነኝ ማለት አይበቃም፡በቃል
በተግባር፡እንየው፡ስራ፡ላይ፡ይዋል
እስቲ ዞር፡ብልን፡ስነምግባር፡እንይ
ነጋዴው፡አታሎ፡ንሰሀ፡ቢግባ
ዝሙት፡አገር፡ገዝቶ፡ሰውን፡ሊያግባባ
ሰው፡ሰውን፡ጠልቶ፡አገር፡ሊገነባ
ፍርደ፡ገምድል፡ሰዎች፡ዳኛ፡በሆኑበት
ብሎግ ገዳም ሆኖ የሚመነዱበት
በፓልቶክ ሜዳላይ የሚሰበኩበት
ወይ እምነት!!
ረሀብትኛ፡ሰዎች፡የሚገረፉብት
ሰው፡አገሩን፡ጠልቶ፡የሚሰደድበት
ወይ፡ኢትዮጵያዊነት!ወይ፡ኢትዮጵያዊነት!
ማን፡አይቶት፡ያየወዳኛው፡አለም
የዚህን፡ሳናውቀው፡እያልን፡ልትም፡ልትም
መጨረሻ የለው፡አንደርስም፡የትም።



DAR_SEBE

1 comment:

Anonymous said...

this is good i think u r frestreted