Friday, March 13, 2009

ታጠቀ፡ ተነሳ፡የፓልቶክ፡ ወታድረ

ታጠቀ፡ ተነሳ፡የፓልቶክ፡ ወታድረ
ሊያጋጭ፡ ሊያፋጭ፡ ሁሉን ሰው እደውር
የፖለቲካ የ እምነት ሰባኪ፡ ባራኪ
በስም አልባ ዜጋ ተራ ሰው ፡ተመኪ
ይኸ ው ዝሆን፡ገባ፡ሊያተራምሰው
የተሰራውን፡ቤት፡ሊየፈራርሰው
ጥላቻውን፡ሊገልዽ ሊሰፋ እምነቱ
ፓልቶክ፡ደረሰለት፡ለማንነቱ
ይህን፡ይመስል ነበር፡በ እምነት፡መጥናቱ
ሴጣን፡የጋለበው፡ የፓልቶክ ሰራዊት
ይህ፡ነው፡ጀብድ ማለት፡ይህ፡ነው፡ትልቅነት
ዘር፡ማጥፊያ፡መዘዝ፡ፈላጊ
በጭፍን፡እምነት፡ተዋጊ
እራስን፡ከመላክ፡መድቦ
ሴጣን፡ሴጣኑን፡አድቦ
የኔ፡ትክክል፡ብሎ፡ተገዝቶ
በ፡እውሸት፡ቤቱን፡አርቅቆ፡መርቶ
ፓልቶክ፡ገባ፡ጎጆውን፡ሊጥል
እሮ፡ወሸባ ዪ፡ሊባል
እውነት፡ተርጎመጎመ፡አበጠ፡ፈነዳ
የባንዳዎች፡መደር፡ሊሰበር፡ሊጎዳ
እውነት፡ትመጣለች፡ጊዜዋን፡ጠብቃ
የፓልቶክ ወታድር፡ከባንዳ፡አጣብቃ
ኢትዮጵያን፡ለ ኢትዮጵያዊ፡የሚል፡አርማ፡አጥልቃ
ጥላቻን፡ፈልቅቃ፡አምቅቃ፡አውልቃ፡
ዳርሰቤ

No comments: