Wednesday, August 29, 2018

ይድረስ ለጠ/ሚ ጽ/ቤት
ሹመቶች ላይ አሳሳች
ጥቆማ እያስተዋልን ነው
================
ጠቅላላ:- የአዲስ አበባ ሹመቶችን አስተውለን ይሆናል እንጂ ኦሮሚያ ክልል ላይ ከተመረጡ አዳዲስ ወደ 20 አመራር ውስጥ ሙስሊሞች ባለቀ ሰዓት 2 ለከፍተኛ 2 ዝቅ ላለ ቦታ ለማስገባት እንደሞከሩ ተረድቻለሁ:: አሁን ላይ ጉርምርምታም አለ:: ምክንያቱም በትግል ወቅት ብዙ ሙስሊም ተሰውቷል:: የአዲስ አበባ የሥራ አስፈጻሚ ሹማምንትም ላይ ከ20ዎቹ 1 ሰው በምክትል ደረጃ ነው የተቀላቀለው::
ይህንን የምለው ቡድንተኛ አስተሳሰብ ተጠናውቶኝ አይደለም:: አምርሬ ከምጠላቸው ነገሮች ውስጥ ነው:: ለክርስቲያን ወንድሞች ,,, ክርስቲያን ከሚበዛበት ከአማራ ክልል 18 ሙስሊም እና 2 ክርስቲያን ቢመጣ ዝም ትሉ ነበር? እንደውም ጭራሽ ሁለት ሙስሊሞች ተገኙ ተብሎ አይደል እንዴ አንዴ ትግሬ ናቸው አንዴ ኦሮሞ ናቸው እየተባለ አጥንት ቆጠራ የተገባው? እና እናንተ ላይ እንዲሆን የማትሹትን ነገር ሌላውም ላይ እንዲሆን የምትሹ አይመስለኝም:: ተዋፅኦ ቀርቷልና በችሎታ ነው ካላችሁን አዳዲሶቹ 16 ሚኒስትሮችን ሙስሊም እናድርጋቸው:: ችሎታ ያለው በርካታ ሙስሊም አለ::
በመሆኑም ፕራይቬታይዜሽን ላይ የተሾሙትን ስናስትውል እና በተለያዩ መግለጫዎች ስንሰማ ከሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል የተውጣጡ ናቸው ተብሏል::
ከመንግሥት ተቋማት ዜናዎች ውስጥ
<<ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በመንግስት ስር ያሉትን ትልቅ የልማት ድርጅቶች ወደ ግል ዘርፋ
ለማዘዋወር የሚያደርገውን ሂደት ግልፅ እና ተጠያቂነት ባለበት መንገድ የሚከታተል 21 አባላት ያሉት የአማካሪ ኮሚቴ አዋቀሩ። እነሱም፦
1 አቶ እየሱስ ወርቅ ዛፍ
2 አቶ ዘላለም መለስ
3 ዶ/ር አለማየሁ ስዩም
4 ወ/ሮ መአዛ ብሩ
5 አቶ በቀለ ገለታ
6 አቶ አበበ አዕምሮስላሴ
7 አቶ ልደቱ አያሌው
8 ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ
9 አቶ በቀለ ገርባ
10 ወ/ሮ ሳራ አበራ
11 ዶ/ር አይናለም መገርሳ
12 ፕሮፌሰር ጣሰው ወ/ሀና
13 ዶ/ር ፀጋዬ በርሄ
14 ዶ/ር ተናዬ ወርቅ ጌቱ
15 አቶ ካሲ ከበደ
16 አቶ ግርማ ሰይፍ
17 አቶ ሌንጮ ባቲ
18 ዶ/ር አብረሃም ተከስተ
19 ዶ/ር ይናገር ደሴ
20 አቶ ተክለወልድ አጥናፍ
21 አምባሳደር ግርማ ብሩ
========
በግሌ አዲሱን ለውጥ በነፃና በፈቃደኝነት በንጹሕ ልብ ለማገልገል ከወሰኑ ሰዎች ነኝ:: እጅግ ደስተኛም ነኝ:: በእስካሁኖቹ ሂደቶች በጣም ደስተኛ ነኝ:: ዘወትርም እያመሰገንኩ ነው:: ነገር ግን ለውጡን የሚያስቀለብሱ አዝማሚያዎችን የማረም ሀገራዊ ኃላፊነት አለብኝ::
በመሆኑም ለጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ የምጠይቀው እኛ ሙስሊሞቹ የቱ ጋር ነን? ምክንያቱም ይህ ሹመት እንጂ በድምፅ አሠጣጥ የመጣ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ አይደለም:: "ግልፅና ተጠያቂነት ባለው መንገድ" ማለትስ ምን ማለት ነው? ክቡር ዶክተር ሆይ ሰዎች እያሳሳቱዎ ነው:: ከ21 ውስጥ አስሩን ሙስሊም ቢያደርጉ ቅር የሚለው አይኖርም ነበር:: 5 ሰውስ እንዴት ጠፋ? ለወሬ ነጋሪ አንድ ሰው እንኳ እንዴት አልተካተተም? አዎ ድርጅቶቹ የጋራችን ናቸው::
እኛም የጋራ ስሜት እንዲሰማን ያድርጉን:: ካልሆነ ግን ግማሽ የሀገሪቷን ሕዝብ አግልሎ ,,, ድርጅቶቹ ሰላማዊ ንግድ ያከናውናሉ ማለት አስቸጋሪ ነው:: ስጋቴን ነው እየገለጽኩ ያለሁት:: ስለዚህ ድጋሚ ያዋቅሩት:: ጠቋሚ ከጠፋ አይደለም 21 ሰው ይቅርና 2000 ሙስሊም አቀርብሎታለሁ:: ግን ይህንንም የማቅረብ ሥልጣን የለኝም:: ተራ ሰው ነኝ:: እንደው እንደዜግነትህ ጠቁም ብባል አጠገብዎ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ወይም የፓርላማ መብራቱ ጋር እነ ዶክተር ፕሮፌሰር ናስር ዲኖ እና ዶክተር ፕሮፌሰር አህመድ አሉልዎ:: (ፈቃደኛ ከሆኑ) እጅግ በጣም ታማኝ, ለግል ኑሯቸው ሞልቶም የተረፋቸው ናቸው:: ከመፍትሔ አፈላላጊ, ከምሁራን, በመንግሥት ቢሮ ካሉ, በፓርቲዎችም ውስጥ ኧረ ብዙ ሰው አለ:: ይህኛው ግን የሆኑ ቡድኖች የሆነ ቦታ ተደራችተው መጥተው ነው የሚመስለው:: ድጋሚ ያዋቅሩት::
[በቅን ልቦና ለውጡን መጠበቅ ግዴታችን ነው]
[ዓብዱልቃዲር ኑረዲን; በፌስቡክ አጻጻፍ ለጥቆማ ያህል በግል የተጠየቀ]

No comments: